February 2020 meeting
የአብረን እንሁን መረዳጃ ማህበር ወራዊ ስብሰባ
ቃለ ጉባኤ
ቀን፣ February 1st , 2020
የስብሰባ ቦታ፣ አቶ ጌትዬ ቤት
ያልተገኙ አባላት፣ 1ኛ አቶ መዘምር
2ኛ አቶ ገመችስ
3ኛ አቶ ዮሴፍ
4ኛ አቶ ከበደ
5ኛ አቶ ክንፈ ናቸው
የእለቱ አጀንዳ
የእለቱ አጀንዳ (Social Security) ጡረታ በተመለከተ መደረግ ያለባቸው ቅድመ ዝግጅቶች፡፡
ስለ (Social Security) የሚያብራሩልን አቶ ቴሶ ቆሳ ሲሆኑ እሳቸውም ስለ (fv Security) ሰፋ ባለ መንገድ አስረድተዋል፡፡ አንድ ሰው ከደመወዙ የሚቆረጥበትን መቼ መውሰድ እንደሚጀምር በእድሜ ልዩነቶቹን አስረድተዋል፡፡ በዚህም መሠረት እድሜው ለጡረታ ሳይደርስ ማለት በ62 አመቱ ቢወጣ ወይም በ66 አመቱ ሙሉ ጡረታውን አስጠብቆ ቢወጣ ያለውን ጥቅሞች እና ጉዳቶቹን በዝርዝር ያስረዱ ሲሆን ከቤቱም የተለያዩ አስተያየቶች ቀርበው በልዩነቶቹ ላይ ተወያይተዋል፡፡ ይህንን ሙሉ መረጃ አቶ ቴሶ በሚልኩት ኢሜል ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡ በአጠቃላይ የተደረገው ውይይት ረዥም በመሆኑ ለሚቀጥለው ወር እንቀጥልበታለን በማለት ሊቀመንበሩ የእለቱን ስብሰባ ዘግተዋል፡፡